Table of Contents
የስራ ስፍራን ለመቀየር የሚረዱ የ ዲዛይን ምክረ_ሃሳቦች
የቢሮ ውስጥ ዲዛይን ምክረ ሃሳብ
እንደሚታወቀው በሃገራችን ላይ የሚገኙ የመንግስት ቢሮዎች እና የንግድ ስራ ቦታዎች ባለፈው ሶስት ዓመት ውስጥ አንዳንድ አስገራሚ የዲዛይን እና የስፍራ ከባቢ ለውጦችን አድርገዋል ፣ ጅማሬው የሚበረታታ ቢሆንም ነገር ግን ገና በሁሉም የስራ ቦታ ላይ መስፋፋት ይጠበቅበታል፡፡ በስራ ስፍራ ላይ ባሉ ቢሮዎች እና ሰራተኞች መካከል ግድግዳዎችን ከማፍረስ ጀምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማቀናጀት ጠንክረው እንዲሰሩ ለማነቃቃት የቤት ውስጥ ዲዛይን (Interior Design) የሚሰጠው ሚና ከፍተኛ ነው። የወደፊቱ የስራ ስፍራ ሰፊ፣ ክፍት፣ ምቹ ፣ አገልግሎት-ተኮር እና የበለጠ ሰራተኛን ለስራ ሚያነሳሳ እንደሚሆን አንጠራጠርም። ስለዚህም የሚከተሉትን የዲዛይን ምክረሃሳቦችን ጀባ ብለናል።
1- ብዙ ግድግዳዎችን መቀነስ
ልቅ ፣ ክፍት እና ቀለል ያሉ የስራ ቦታዎች በ 2021 በአለማችን የተለመዱ ሆነዋል። ይህም የሚከተሉትን የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጠናል
- የስራ ፍጥነትን እና ጥራትን ይጨምራል
- ክፍት የስራ ስፍራ የተሻለ የሰራተኞችን የመግባባት ባህሪን ይጨምራል
- የስራ ግልጽነትን እና እምነትን ይጨምራል
60 % የሚሆኑት አለማችን ላይ የሚገኙ ድርጅቶች ክፍት የሆነውን የቢሮ አቀማመጥ ዘዴ መጠቀም ጀምረዋል ። እርስዎም መተግበር ቢጀምሩ መልካም ነው።
2 _ የስራ እንቅስቃሴን እና አካላዊ ባህርይን ያማከለ ስፍራ መፍጠር
Ergonomics ( የአካላዊ እና ስፍራ መስተጋብር ) ማለት በእኛ ሰዎች እና በምንኖርበት ዓለም መካከል ያለውን መስተጋብር የሚስተበሩባችው መንገዶች ላይ ያተኮረ የሳይንስ ዓይነት ነው፡፡ በቤት ውስጥ ዲዛይን Ergonomics ሲተገበር ዲዛይኑን የበለጠ ለተጠቃሚ ምቹ እና ስራን ቀልጣፋ ለማድረግ ይረዳል ፡፡
በአካላዊ መስተጋብር-አስተሳሰብ የተሰሩ ውስጣዊ ንድፍ ለመኖር “ቀላል” ብቻ ሳይሆኑ በሚሰጡት ምቾት ምክንያት “ደስተኛ” የስራ ስፍራን እና ስራን በቀላሉ ለመምራት የሚረዳ የመስሪያ ቦታዎችን ይሰጡናል ፡፡ የቢሮ እና የስራ ስፍራ ውስጣዊ ዲዛይን የተገልጋዮችን አካላዊ ባህሪ መሰርት በማድረግ ከተሰራ የሰራተኞችንም ሆነ የደንበኛን ምቾት ጠብቆ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ይረዳል፡፡
3_ የእቃ መጨናነቅን መቀነስ
የሥራ ስፍራቸው ከተለያዩ እቃዎች መዝረከረክ ነጻ በሚሆንበት ጊዜ ሠራተኞች በስራቸው ላይ የበለጠ ማተኮር ፣ የበለጠ ውጤታማ መሆን እና በጥልቀት ስራን በመፈፀም ረገድ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል ፡፡
4_ የቢሮ ውስጥን በውጭ ተክሎች ማዋሃድ
ዎች ከተፈጥሮ ጋር የተገናኘ የመሆን ውስጣዊ ፍላጎት አላቸው ፡፡ ሳይንቲስቶች እና ሳይኮሎጂስቶች ቢዮፊሊያ በመባል የሚታወቀውን ይህን ክስተት ለአስርተ ዓመታት መዝግበዋል ፡፡ የፀሐይ ብርሃን እና የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮችን ማግኘት ፣ ለምሳሌ በመስኮት ውጭ ያሉ ዛፎች ወይም በቢሮ ውስጥ ያሉ ህያው እፅዋቶች ሰራተኞች በስራቸው ደስተኛ እና የበለጠ ውጤታማ ያደርጓቸዋል ፡፡
የዓለም አረንጓዴ ህንፃ ምክር ቤት በስራ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ስምንት የሥራ ሁኔታዎችን ተከታትሎ የጥናት ጽሁፍ አቅርቦ ነበር ፡፡ እነዚህም የአየር ጥራት ፣ የአየር ሙቀት መጠን ፣ የመስኮቶች ቅርበት ፣ የተፈጥሮ ዕይታዎች ፣ የህንፃው ገጽታ እና ስሜት እና ሌሎችም በስራ ላይ ተጸእኖ ይፈጥራሉ ያላቸው ናቸው ፡፡ ጥናቱ እንደሚያሳየው እነዚህን ምክንያቶች ማሻሻል የበለጠ ንቁ ፣ ውጤታማ ፣ ለሥራቸው ታማኝ እና ሥራን በፍጥነት እና በጥራት የማውጣት ዕድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ሠራተኞችን አስገኝቷል ፡፡
በቢሮው ውስጥ ያሉት አረንጓዴ ተክሎች አየርን ለማፅዳትም ሊረዱ ይችላሉ ፡፡ ስለዚህ እፅዋትን በቢሮ ውስጥ ሲያስቀምጡ እጽዋትን መንከባከብ ሰራተኞች ተራ በተራ እንዲያደርጉት ፣ ወይም በተቀመጠ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተክሎችን የሚንከባከቡ ሰራተኞችን ወይም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ይቀጥሩ ፡፡ ሰው ሰራሽ እጽዋት እንኳን የሥራ ቦታን ገጽታ ለእይታ ብቻ ሊቀይሩት ይችላሉ፡፡ ሰው ሰራሽ እጽዋቶችን መጠቀም ለእንክብካቤ የሚዎጡ ወጪዋችን ሊቀንሱ ይችላሉ። ነገር ኝ እንደ ተፈጥሮ እጽዋቶች ያክል አስተዋጣኦ ኝ አይኖራችውም።
Sources:
http://www.jll.com/Documents/csr/Workplace-design -and-practices-on-the-ethical-environment.pdf
http://www.cnbc.com/id/48488208
http://greenplantsforgreenbuildings.org/
http://multivu.prnewswire.com/mnr/officemax/46659/docs/46659-NewsWorthy_Analysis.pdf
http://www.facilitiesnet.com/ceilingsfurniturewalls/article/- Sustainable-Design-FIexibility-Mobility-Are-Key-Selection-Criteria-for-Office-Furniture- – 13209#
http://ehstoday.com/health/ergonomics/ehs_imp_38484
http://ayearofproductivity.com/angela-wright-interview/
http://www.jll.com/Documents/csr/Workplace-design -and-practices-on-the-ethical-environment.pdf
http://www.cnbc.com/id/48488208
http://greenplantsforgreenbuildings.org/
http://multivu.prnewswire.com/mnr/officemax/46659/docs/46659-NewsWorthy_Analysis.pdf
http://www.facilitiesnet.com/ceilingsfurniturewalls/article/- Sustainable-Design-FIexibility-Mobility-Are-Key-Selection-Criteria-for-Office-Furniture- – 13209#
http://ehstoday.com/health/ergonomics/ehs_imp_38484
http://ayearofproductivity.com/angela-wright-interview/



